Ethiopians- Protest At Saudi Arabia embassy In Stockholm

Sad Ethiopian Message from Saudi Arabia, የወገኖቻችን የድረሱልን ጥሪ ከሳኡዲ አረቢያ

የኢትዮ-ካናዳውያን የእርዳታና ትብብር ድርጅት፥

ይህ ድርጅት እንዲመሰረት በዋናነት ካነሳሱን ጉዳዮች ውስጥ፥ 

በሳዑዲ ዓረቢያና በተለያዩ ክፍለ ዓለማት በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ያለው ሰቆቃ፣ በአገር ውስጥና በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ትልቅ የመነጋገሪያ ጉዳይ ሆኖ የሰነበተው ማለቂያ የሌለው የሕዝባችን ፍዳ ለመሆኑ ለማንኛችንም የተሰወረ ሚስጥር ዓይደለም:: ሰሞኑን በሳዑዲ ዓረቢያ በወገኖቻችን ላይ የተፈጸመው ግፍና መረን የለቀቀ ሕዝባዊ በደል፥ ኃይማኖትን ጎሳንና የፓለቲ ዓመለካከትን ሳይለይ በአጠቃላይ በኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ ያነጣጠረ ብሔራዊ ውርደት፥ የእያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ ህሊና ያንኳኳ፣ ቆም ብለን ራሳችንን እንድንጠይቅ ያስገደደና አጣዳፊ ምላሽ የሚያስፈልገው በሕልውናችን ላይ የተቃጣ ፈታኝ ዓደጋ በሕብረተሰባችን መካከል ከፍተኛ ጥያቄ ሆኖ ሰንብቷል::

በዓጠቃላይ በመካከለኛው ምስራቅ አገሮች፥ በተለይ በሳዑዲ ዓረቢያ በተለያዬ ምክንያትና ባገኙት መንገድ ገብተው እራሳቸውንና ቤተሰባቸውን ለመርዳት በተሰደዱ ኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ያለው እጅግ አሰቃቂ ግፍና መከራ ሁላችንን ከማሳዘኑም በላይ፤ ፖለቲካ፣ ጎሳና እምነት ሳይለያየን ከመቼውም በበለጠ በመሰባሰብ ለጋራ ህልውናችን በጋራ መነሳትና በዓንድነት መፍትሄ መሻት እንዳለብን ያሳሰበ አስደንጋጭ ደወል ነው። ወገለወገ ፈጥኖ መድረስም ሰብዊና የዜግነታችን ግዴታ መሆኑን ለብዙዎች ያስገነዘበ፥ በሌላም አገራዊና ሰብዊ ጉዳዮች ላይ መተባበር እንዳለብን ተረድተን የዓስተሳሰብ ለውጥ እንድናደርግ ትልቅ ተጽዕኖ ለማድረጉ ሰሞኑን ያለምንም ቀስቃሽና ጉትጎታ በዓለም ዓደባባዮች በተከታታይ የታየው ትዕይንተ ሕዝብና የተሰማው የኢትዮጵያውያን የድረሱልን ጥሪ ብቸኛ ምስክር ነው 

ስለሆነም በቶሮንቶና በአካባቢው የምንኖር ኢትዮጵያውያን ይህንን የመሰለና ሌላም የጋራ ችግሮቻችንን ለማስወገድ ተባብረን እንድንሠራ “ኢትዮ-ካናዳውያን የእርዳታና ትብብር ድርጅት” አቋቁመናል። ዓላማውም በወገኖቻችን ላይ የተፈጸመውን ሰቆቃና እየደረሰ ያለውን ግፍና መከራ ወደፊትም ሊደረስ የሚችለውን በሕዝባችን ላይ የተቃጣ አደጋ ግምት ውስጥ በማስገባት፥ ለወገን የድረሱልን ጥሪ ምላሽ መስጠት የሚያስችል ሁሉን ዓቀፍ የሆነ የእርዳታና የትብብር መድረክ መመስረት ሲሆን፥ በDecember 15, 2013 በተደረገው ሕዝባዊ ስብሰባ ኢትዮ-ካናዳውያን የእርዳታና ትብብር ድርጅት በሚል ስም ተቋቁሞ፣ የዓጭርና የረጅም ጊዜ እቅዶችን አውጥቶ፣ በሕዝባችን ላይ ለሚከሰቱ ወቅታዊ ችግሮች መፍትሄዎችን ለመሻት እንቅስቃሴውን በይፋ ጀምሯል::

ይህ ድርጅት በሕዝብ የተመረጡ ሰባት የስራ ዓስፈጻሚ ኮሚቴና ሶስት አማካሪ ዓባላትን ያካተተ፥ አስር የዓመራር ዓካላት ሲኖሩት ከሌሎች መሰል እህት ድርጅቶች ጋር በመመካከርና በመረዳዳት በዘላቂነት የሚሰራ፥ የኢትዮጵያውያንን ችግር በኢትዮጵያውያን ለመፍታት የተቋቋመ፣ ለማንኛውም ኢትዮጵያዊ ክፍት የሆነ የእርዳታ ድርጅት እንደመሆኑ መጠን፥ ለሰብአዊ መብትና ፍትህ ተቆርቋሪ የሆነ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ዓላማውን ተረድቶ አቅሙን ለማጎልበት በመሳተፍ አስተዋፅዖ ማድረግ እንዲችል ጥሪ እናደርጋለን። 

ኤትዮ-ካናዳውያን የእርዳታና ትብብር ድርጅት የጊዜው አፋጣኝ ትኩረትና የመጀመሪያ ስራው በቅርቡ በተቋቋመው “ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት” በኩል ችግር ለገጠማቸው ኢትዮጵያውያን እርዳታ ለመለገስ አጣዳፊ መርሃ ግብር ዓውጥቶ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ምሽት በማዘጋጀት ላይ ይገኛል፤ ለዚህ በጎ ተግባርም በቶሮቶና አካባቢው የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ሁሉ ተሳታፊ በመሆ ለወገኖቻችን የተቻላቸውን ይረዱ ዘንድ እንዲተባበሩን በትህትና እንጠይለን።