Acknowledgment of Receipt, Letter from Swiss Confederation ከስዊዝ መንግሥት የተላከ የመልስ ደብዳቤ

Recently, ECRCO organized and collected signatures, online and in public places calling for Fair and Free trial of Co-pilot Hailemedhin Abera Tegegn to Petition the Swiss Government in support of his asylum case and we successfully delivered significant number of signatures with protest letter to the Swiss Embassy in Ottawa, Canada and we would like to say thank you to all who participated in this task.
Letter from the Swiss Confederation, Federal Chancellery Political Rights Section
ሰሞኑን በድርጅታችን ዓስተባባሪነት የረዳት ፓይለት ኃይለመድህን ዓበራ ተገኝን የስደተኝነት ጥያቄ በተመለከተ፥ 
የኢትዮጵያን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ በማገናዘበ ሕጋዊ ከለላ እንዲደረግለትና የማንም ተጽዕኖ የሌለበት ፍትሃዊ ፍርድ እንዲያገኝ ይገባዋል በማለት፥  በማህበራዊ ቦታዎችና በኢንተርኔት በመታገዝ የተሰበሰቡ በርካታ የምልጃ ፊርማዎችና፥ የኢትዮጵያን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ በመዘርዘር የጉዳዩን ክብደት ከሚጠቁም የድጋፍ ደብባቤ ጋር ለስዊዘርላንድ መንግስት በኢምባሲው ዓማካይነት መላካቻን ይታወቃል፥ 
የላክነው መልዕክትም ወደሚመለከተው ክፍል መድረሱን የሚያረጋገጥ ምላሽ ይዞ ከዚህ በታች የሚታየውን ደብዳቤ ከስዊዘርላንድ መንግስት ዓግኝተናል፥ ሁኔታው የደረሰበትን ደረጃም እስከመጨረሻው እንደምንከታተል ቃል እየገባን፥ ለዚህ የተቀደሰ ተግባር ለተባበራችሁን ሁሉ ምስጋናችን ከፍ ያለ ነው፥

Switzerland Embassy Letter to ECRCO Concerning Co-pilot Hailemedhin Abera Tegegn' case

Recently, ECRCO organized and collected signatures, online and in public places calling for Fair and Free trial of Co-pilot Hailemedhin Abera Tegegn to Petition the Swiss Government in support of his asylum case and we successfully delivered significant number of signatures with protest letter to the Swiss Embassy in Ottawa, Canada and we would like to say thank you to all who participated in this task.
This is the letter from the Ambassador of Switzerland Confederation in Ottawa, Canada;
ሰሞኑን በድርጅታችን ዓስተባባሪነት የረዳት ፓይለት ኃይለመድህን ዓበራ ተገኝን የስደተኝነት ጥያቄ በተመለከተ፥ 
የኢትዮጵያን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ በማገናዘበ ሕጋዊ ከለላ እንዲደረግለትና የማንም ተጽዕኖ የሌለበት ፍትሃዊ ፍርድ እንዲያገኝ ይገባዋል በማለት፥  በማህበራዊ ቦታዎችና በኢንተርኔት በመታገዝ የተሰበሰቡ በርካታ የምልጃ ፊርማዎችና፥ የኢትዮጵያን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ በመዘርዘር የጉዳዩን ክብደት ከሚጠቁም የድጋፍ ደብባቤ ጋር ለስዊዘርላንድ መንግስት በኢምባሲው ዓማካይነት መላካቻን ይታወቃል፥ 
የላክነው መልዕክትም ወደሚመለከተው ክፍል መድረሱን የሚያረጋገጥ ምላሽ ይዞ ከዚህ በታች የሚታየውን ደብዳቤ ከስዊዘርላንድ መንግስት ዓግኝተናል፥ ሁኔታው የደረሰበትን ደረጃም እስከመጨረሻው እንደምንከታተል ቃል እየገባን፥ ለዚህ የተቀደሰ ተግባር ለተባበራችሁን ሁሉ ምስጋናችን ከፍ ያለ ነው፥

Fundraising Event የገንዘብ ማሰባሰቢያ ምሽት፥

የገንዘብ ማሰባሰቢያ ምሽት በቶሮንቶ፥

በሳኡዲ ለተፈናቀሉ ኢትዮጵያውያን እርዳታ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ምሽት በተሳካ  ሁኔታ ተካሂዷል፥
በቶሮንቶ እና በዓካባቢዋ የሚኑሩ፥ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለወገኖቻቸው መከታ መሆናቸውን በዓስቸጋሪው የካናዳ የክረምት ምሽት በሮዶውና ብርዱ ሳያግዳቸው በዕለቱ በተደረገው የዕራት ግብዣ ላይ ተገኝተው፥ በቅርቡ በተቋቋመው ዓለም ዓቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት ድርጅት በኩል ለመርዳት በዝግጅታችን ላይ በመገኘት በሞራል ድጋፍና እጃቸውን በመዘርጋት የወገኖቻቸው ጋሻ መሆናቸውን ዓስመስክረዋል፥
ይህን የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በስኬታማነት ለማከናወን ውድ ጊዜዓቸውንና ገንዘባቸውን በመለገስ ለተባበሩን ግለሰቦችና የንግድ ተቋማት እንዲሁም በሙያቸው በግል በመነሳሳት ድጋፍ ላደረጉልን ወገኖቻችን ከፍ ያለ ምስጋና ልናቀርብ እንፈልጋለን፥
የተሰበሰበውም ገንዘብ በመገናኛ ብዙሃን እንደተገለጸው ከወጭ ገቢ ተስተካክሎ ምን ያክል ገንዘብ ወደተረጅዎች እንደደረሰ በቅርቡ እናሳውቃለን፥