በሳኡዲ ለተፈናቀሉ ኢትዮጵያውያን እርዳታ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ምሽት በተሳካ ሁኔታ ተካሂዷል፥
በቶሮንቶ እና በዓካባቢዋ የሚኑሩ፥ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለወገኖቻቸው መከታ መሆናቸውን በዓስቸጋሪው የካናዳ የክረምት ምሽት በሮዶውና ብርዱ ሳያግዳቸው በዕለቱ በተደረገው የዕራት ግብዣ ላይ ተገኝተው፥ በቅርቡ በተቋቋመው ዓለም ዓቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት ድርጅት በኩል ለመርዳት በዝግጅታችን ላይ በመገኘት በሞራል ድጋፍና እጃቸውን በመዘርጋት የወገኖቻቸው ጋሻ መሆናቸውን ዓስመስክረዋል፥
ይህን የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በስኬታማነት ለማከናወን ውድ ጊዜዓቸውንና ገንዘባቸውን በመለገስ ለተባበሩን ግለሰቦችና የንግድ ተቋማት እንዲሁም በሙያቸው በግል በመነሳሳት ድጋፍ ላደረጉልን ወገኖቻችን ከፍ ያለ ምስጋና ልናቀርብ እንፈልጋለን፥
የተሰበሰበውም ገንዘብ በመገናኛ ብዙሃን እንደተገለጸው ከወጭ ገቢ ተስተካክሎ ምን ያክል ገንዘብ ወደተረጅዎች እንደደረሰ በቅርቡ እናሳውቃለን፥
No comments:
Post a Comment