FREE ANDARGACHEW TSIGE TASKFORCE, Protest Ottawa

በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በወያኔ እጅ መውደቅና የየመን መንግሥት ለጠላት ዓሳልፋ ሥትሰጠው የኢንግሊዝ መንግሥት በቸልተኛነት መመልከቷን በመቃወም፥ በትናንትናው ዕለት July 8, 2013 በኦታዋ ካናዳ ከፍተኛ ቁጭትና ቁጣ የተሞላበት ሰላማዊ ሰልፍ ተደረገ፥
የኦታዋ ከተማ ዓንዳርጋቸው ጽጌ በዓስቸኳይ ይለቀቅ በሚሉ የዓንዳርጋቸው ጽጌን የትግል መንፈስ በተላበሱ ኢትዮጵያውያን ስትናጥ ውላለች፥

በ FREE ANDARGACHEW TSIGE TASKFORCE TORONTO ቡድን ዓሰባሳቢነት ከቶሮንቶና ዓካባቢው ከተማዎች ተጠራርተው በእረጅም የዓውቶቡስ ጉዞ፥ ለአንች ነው አገሬ የሚለውን ቀስቃሽ ዝማሬ እየዘመሩ በመጡ የኢትዮጵያ ልጆች የተመራው ነጻነት ለዓንዳርጋቸው ግብረኃይል እሳት ለብሶ እሳት ጎርሶ ከሚጠብቀው የኦታዋና ዓካባቢዋ ነዋሪ ኢዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያን ጋር በመተባበር፥ የፖለቲካ ፓርቲ፣ የዘር ድርጅትና ኃይማኖት ሳያግድቻቸው በአንድነት ድምጻቸውን ከፍ ዓድርገው፥
We are Andargachew Tsige!
Free Andargachw Tsige!
Andargachew is our Mandela!
Britain where is your Citizen Andargachew Tsige?
እና ሌሎችም ተመሳሳይ መፈክሮችን ዓንግበው፥ የእንግሊዝን ኢምባሲና በኢትዮጵያ ስም የሚጠራውን የወያኔ ኢምባሲ ሲያስጨንቁት ውለዋል፥
በሰልፉ የሚታየው ሁኔታ እጅግ ቁጣ የተቀላቀለበት በየመን መንግሥትና በወያኔው የማፊያ ቡድን ላይ ከፍተኛ የበቀል ስሜትን ያዘሉ የቁጭት መልክቶች የተላለፈበት ትዕይነተ ሕዝብ ነበር፥
የእንግሊዝንም መንግሥት ይህ ሚስጥር ያለበት በሚመስል መልኩ የትውለደ ኢትዮጵያዊ ዜጋዋን መብት የዓለማስከበርና በቸልተኛነት የመያዝ ነገር ዓድልዋዊ እንደሆነ በማሳሳብ በዓጽንኦት ዓውግዘዋል፥
በመጨረሻም ለብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስቴርና በካናዳ ለሚገኘው ዓምባሳደር በግብረ ኃይሉ የተዘጋጀውን ደብዳቤ በዕጅ ካላስረከብን ሰልፈኛው ከዚህ ዓይሄድም በማለት የእንግሊዝ ኢምባሲ ተወካዩን ልኮ ወደ ሚገባው ቦታ እንደሚያደርሱ ቃል ከገቡልን በኋላ፥
ወደ ኢትዮጵያው የወያኔ ኢምባሲ ሰልፈኛው ተጉዞ፥ በኢምባሲው ፊት ለፊት የየመንና የኢትዮጵያ የውንብድና ስራ የማያድን ጋሻ ጎን ያሰብራል እንደተባለው በከንቱ በመወዳጀት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የፈጸሙት በደልና ሰንካላ ድፍረት በጊዜውና በሰዓቱ ከባድ ዋጋ እንደሚያስከፍላቸው በማሳሰብ፥ TPLF Free our Hero Andargachew! Canada Close Ethiopian Embassy!
በሚል ጽኑዕ ቁጣ ሰልፈኛው የየመንን ባንዴራ ከመሬት እየረገጠ ሰልፉ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል፥
ከዚህ በኋላ ወያኔዎች ዓንዳርጋቸውን የሚለቁት ለዕራሳቸው ሲጨንቃቸው እንጂ ለዕኛ ዓዝነው ዓይደለም፥ የዓንዳርጋቸው የዓርበኛነት መንፈስ በሕዝቡ ደምና ዓጥንት የገባ በወያኔ ላይ ካልፈነዳ የማይበርድ እንደ እሳተ ገሞራ ያለ ታላቅ ኃይል ነው፥
ታጋይ ይወድቃል ትግል ይቀጥላል፥ የኢትዮጵያ የነጻነት ቀን ቀርቧል፥
ኢትዮጵያ በቆራጥ ልጆቿ ተጋድሎ ነጻ ትወጣለች፥

No comments:

Post a Comment