ማስታወቂያ
አገራችን ኢትዮጵያ ባለፉት አምሳ ዓመታት ባጋጠማት ተደጋጋሚ ችጋር ብዙ
ዜጎቿን አጥታለች።
ዛሬም እንደገና፥ ከሃያ ሚሊዮን የሚበልጡ ወገኖቻችን ለርሃብ ተጋልጠው፥ ህፃናት፣ እናቶችና፣ ደካማ አዛውንቶች፣ እንስሳቶችን ጨምሮ በርሃብ እየሞቱ ቢሆንም፥
በገጠመን ውስብስብ አገራዊ ችግር ምክንያት ርሃብተኞች በቂ ትኩረት ተነፍጓቸው ሚሊዮኖች በሞት አፋፍ ላይ ይገኛሉ።
ውድ የቶሮንቶና የአካባቢው ነዋሪዎች!
ወገኖቻችን በርሃብ እየረገፉ ዝም ብለን እንድንቀመጥ አላስቻለንምና ፌብሩዋሪ 6 ቀን 2016 ዓ ም፥
ከ2:00pm ጀምሮ የእርዳታ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ተዘጋጅቷል፥
አድራሻው 958 Broadview
Ave. Toronto Ontario
እርስዎም በስፍራው ተገኝተው
ለወገኖችዎ የቻሉትን በመርዳት ሃላፊነትዎትን እንዲወጡ በዓክብሮት ተጋብዘዋል።
የመዝናኛ ሙዚቃ፣ ምግብና መጠጥ ተዘጋጅቷል፥ የሃይማኖት አባቶችና ታዋቂ ግለሰቦች በሚገኙበት የችግሩን ዘላቂ መፍትሄም እንወያያለን።
የመግቢያ ዋጋ $50 ዶላር ብቻ ሲሆን
ትኬቶችን በኢትዮጵያውያን ሬስቶራንቶችና ሱቆች እንዲሁም በዝግጅት ኮሚቴ አባላት እጅ ይገኛሉ።
እንዳይረሱ፥ February 6, 2016
ዓ. ም ቅዳሜ፥ በ 2 ሰዓት
958 Broadview Ave. Broadview subway ዓጠገብ በሚገኘው ዓዳራሽ እንገናኝ፥
የኢትዮ-ካናዳውያን ትብብርና እርዳታ ድርጅት። በቶሮንቶ